ይዌድስዋ መላእክት
Geez
ይዌድስዋ መላእክት
፩: ይዌድስዋ መላእክት ለማርያም በዉስተ ዉሥጤ መንጦላዕት፡ ወይበልዋ በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ። ይቤላ መልአክ ለማርያም ተወከፈዮ ለቃል ኅቤኪ ይመጽእ ወበማኅፀነ ዚአኪ የኅድር፡ እፎ ቤተ ነዳይ ኅደረ ከመ ምስኪን እምሰማያት ወረደ ላዕሌሃ ፈቲዎ ሥነ ዚአሃ ወተወልደ እምኔሃ።
፪: ወበሳድስ ወርኅ ተፈነወ ገብርኤል መልአክ እምኅበ እግዚአብሔር ኅበ አሐቲ ሀገር ዘገሊላ እንተ ስማ ናዝሬት ኅበ ድንግል እንተ ተፍኅረት ለብእሲ ዘስሙ ዮስፍ ዘእምቤተ ዳዊት፡ ወስማ ለይእቲ ድንግል ማርያም፡ ቦአ መልአክ ኅቤሃ ወይበላ ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልእተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ፡ ብርክት አንቲ እምአንስት ወርእያ ደንገፀት እምቃሉ ወሐለየት ወትቤ፡ እፎኑ ከመዝኑ እንጋ አምኃ ይትአምኁ ወይበላ መልአክ ኢትፍርሂ እስመ ረከብኪ ሞገሰ ብኅበ እግዚአብሔር ወናሁ ትፀንሲ ወትወልዲ ወልደ ወትሰምዩዮ ስሞ ኢየሱስ ዉእቱ ዐቢይ ወይትሰመይ ወልደ እግዚአብሔር ልዕል። ወይሁቦ እግዚአብሔር አምላክ መንበረ ዳዊት አቡሁ።ወይነግሥ ለቤተ ያዕቆብ ለዓለም ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግስቱ፡ ትቤሎ ማርያም ለመለክ እፎኑ ይከዉነኒ ዘንቱ እንዘ ኢየአምር ብእሴ እፎኑ ይከዉነኒ አዉሥኦ መልአክ ወይበላ መንፈስ ኢግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽእ ልዕሌኪ ወኃይለ ልዑል ይጸልለኪ ዘኒ ይትወለድ እምኔኪ ቅዱስ ዉእቱ ወይሰመይ ወልደ እግዚአብሔር ልዑል፡ ወናሁ ኤልሳቤጥኒ እንተ እመአዝማድኪ ይእቲ ፀንሰት ወረከበት ወልደ በልኅቃቲሃ ወበርሥዐቲሃ ፡ ወናሁ ሳድስ ዝንቱ ወርኅ ለእንተ ይብልዋ መካን እስመ አልቦ ነገር ዘአይሰአኖ ለእግዚአብሔር፡ ትቤሎ ማርያም ለመለክ ነየ አመቱ ለእግዚአ ኩሉ ነየ አመቱ።ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ።
፫: ይቤላ መልአክ ሰላም ለኪ፡
ይቤላ ግብርኤል ሰላም ለኪ፡
ማርያም ድንግል ሰላም ለኪ፡
ወላዲተ አምላክ ሰላም ለኪ፡
ማርያም ቅድስት ሰላም ለኪ፡
ማርያም ዉድስት ሰላም ለኪ፡
ማርያም ፍሥሕት ሰላም ለኪ፡
ማርያም ብፅዕት ሰላም ለኪ፡
ማርያም ቡርክት ሰላም ለኪ፡
ማኅደረ መለኮት ሰላም ለኪ፡
ደብተራ ፍጽምት ሰላም ለኪ፡
እኅተ መላእክት ሰላም ለኪ፡
ወእመ ኩሉ ሕዝብ ሰላም ለኪ፡
እግዚእትነ ማርያም ሰላም ለኪ፡
ሰላማዊት ሰላም ለኪ፡
ቀደሰኪ ለማህደሩ ልዑል ሰላም ለኪ፡
አብደረኪ ወኅረየኪ ከመ ትኩኒዮ ማኅደሮ ሰላም ለኪ፡
በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት ሰላም ለኪ።
ክንፈ ርግብ በቡሩር ዘግቡር ሰላም ለኪ፡
ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ ማርያም ሥርጉት ሰላም ለኪ፡
ኆኅተ ምሥራቅ ወእሙ ለብርሃን ሰላም ለኪ፡
ትበርሂ እምፀሓይ ወትትሌዐሊ እምአድባር ሰላም ለኪ፡
ማርያም ኅርት ወክብርት ሰላም ለኪ፡
ሰአሊ ለነ ኅበ እግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ከመ ያድኅነነ እመ ይመጽእ በስብሐተ አቡሁ ምስለ መላእክቲሁ ቅዱሳን፡ እመ ያቀዉም አባግዐ በየማኑ ወአጣሌ በፀጋሙ፡ ያቁመነ በየማኑ ምስለ እስጢፋኖስ ሰማዕት ወየዉሓንስ መጥመቅ።ወምስለ ኩሎሙ ቅዱሳን ወሰማዕት ለዓለመ ዓለም አሜን።
Amharic
ይዌድስዋ መላእክት
፩፤ መላእክት ማርያምን በመንጦላዕት ውስጥ ያመሰግኗታል፤ ሐዳስ ጣዕዋ ላንቺ ምስጋና ይገባሻል እያሉ። መልአክ ማርያምን ቃልን ተቀበይው አላት ካንቺ ዘንድ ይመጣልና በማኅፀንሽም ያድራል። እንዴት ከድሀ ቤት አደረ እንደ ምስኪን ከሰማያት ወርዶ የርስዋን ባሕርይ ባሕርይ አድርጎ ተወለደ?
፪፤ በ፮ኛው ወር ገብርኤል መልአክ ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ ተላክ ካንዲት አገር ናዝሬት ገሊላ ከምትባል ለዮሴፍ እጮኛ ከሆነች ከድንግል ዘንድ። የዚች የድንግል ስሟ ማርያም ነው መልአኩ ወደ እርስዋ ገብቶ እንዲህ አላት ደስታ ይገባሻል እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ሰው ሆኗልና ከሴቶች ይልቅ አንቺ ቡርክት ነሽ። ከቃሉ አነጋገር አይታ ደነገጠች እንዲህም አለች እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ ይደረግልኛል? መልአክ እንዲህ አላት ማርያም ሆይ አትፍሪ ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና እነሆ ትፀንሻለሽ ትወልጃልሽ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ እርሱም ታላቅ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል እግዚአብሔር አምላክም የዳዊት ያባቱን ዙፋን ይሰጠዋል እርሱም በያዕቆብ ወገን ለዘላለሙ ይነግሣል መንግሥቱም አያልፍም፤ ማርያምም መልአኩን እንዲህ አለችው ይህ ነገር እንደምን ይሆንልኛል እንዘ ኢየአምር ብእሴ መልአኩም እንዲህ አላት፤ መንፈስ ቅዱስ ይጠብቅሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል ይህ የሚወለደው ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው እነሆ ኤልሣቤጥ ካንቺ ወገን የምትሆን ከሸመገለች ካረጀች በኋላ ፀነሰች ልጅም አገኘች እነሆ ይህ ስድስት ወር ሆነ መካን ሲሏት ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ማርያምም መልአኩን እንደ ቃልህ ይደረግልኝ እኔ ለእግዚአብሔር ባሪያው ነኝ አለቸው።
፫፤ መልአኩ ገብርኤል ማርያም ድንግል ላንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል አላት።
ወላዲተ አምላክ ክብር ምስጋና ይገባሻል፣ቅድስት ነሽና ክብር ምስጋና ይገባሻል፣
የመለኮት ማደሪያ ነሽና ክብር ምስጋና ይገባሻል፣
የተሸለምሽ ድንኳን ነሽና ክብር ምስጋና ይገባሻል፣
የመላእክት እኅት የሕዝቡ ሁሉ እናት ነሽና ክብር ምስጋና ይገባሻል፣
የሁሉ እመቤት ማርያም ክብር ምስጋና ይጋባሻል፣
የሁሉ ሰላም ማርያም ክብር ምስጋና ይገባሻል፣
ልዑል ማደሪያው ትሆኝ ዘንድ መርጦሻልና ክብር ምስጋና ይገባሻል፣
በወርቅ የተሸለምሽ የርግብ ክንፍ በብር ያጌጥሽ ክብር ምስጋና ይገባሻል፣
ጎኖችሽ በወርቅ አመልማሎ የተሸለሙ ላንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል፣
የምሥራቅ ደጃፍ የብርሃን እናቱ ላንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል፣
ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበሪ ክብርሽ ከአድባራቱ ሁሉ ከፍ ከፍ ያለ ላንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል፣
ማርያም ሆይ ከተመረጡ የተመረጥሽ ከተከበሩ የተከበርሽ ላንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል፤
ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ለምኝልን ያድነን ዘንድ ከአባቱ ምስጋና ከቅዱሳን መላእክቶቹ ጋር በመጣ ጊዜ ጻድቅንን በቀኙ ኃጥአንን በግራው ባቆመ ጊዜ እኛን ከሰማዕት እንጢፋኖስ ከመጥምቁ ዮሐንስ እና ከሁሉ ቅዱሳን ከሰማዕታትም ጋር ያቆመን ዘንድ ለምኝልን ለዓለመ ዓለም አሜን፤ ለዘለዓለሙ ይቅር ይበለን።